መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ። - 1 Chronicles
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
1
፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
2
፤ ዳዊትም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን ባረከ።
3
፤ ለእስራኤልም ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፤ አንዳንድም ቍራጭ ሥጋ፥ አንዳንድም የዘቢብ ጥፍጥፍ አካፈለ።
4
፤ በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት ያገለግሉ ዘንድ፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ይወድሱት ዘንድ፥ ያመሰግኑትና ያከብሩትም ዘንድ ከሌዋውያን ወገን አቆመ።
5
፤ አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።
6
፤ ካህናቱም በናያስና የሕዚኤል በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁልጊዜ መለከት ይነፉ ነበር።
7
፤ በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ እጅ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ትእዛዝን ሰጠ።
8
፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙን ጥሩ፤ ለአሕዛብ ሥራውን አውሩ።
9
፤ ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
10
፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
11
፤ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
12
፤
13
፤ ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም የአፉንም ፍርድ።
14
፤ እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው። ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
16
፤ ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
17
፤ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤
18
፤ እንዲህም አለ። ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤
19
፤ ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።
20
፤ ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
21
፤
22
፤ የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
23
፤ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ።
24
፤ ክብሩን ለአሕዛብ፥ ተአምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ።
25
፤ እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው።
26
፤ የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
27
፤ ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው።
28
፤ የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ኃይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
29
፤ ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
30
፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንቶአል።
31
፤ ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሴትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል። እግዚአብሔር ነገሠ በሉ።
32
፤ ባሕርና ሞላዋ ትናወጥ፤ በረሀ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ።
33
፤ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥ የዱር ዛፎች በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል።
34
፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
35
፤ የመዳናችን አምላክ ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ ሰብስበህ ታደገን በሉ።
36
፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ።
37
፤ እንዲሁም በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር ያገለግሉ ዘንድ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድኤዶምንም፥ ስድሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
38
፤ የኤዶታምም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ በረኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋቸው።
39
፤ ካህኑም ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
40
፤ ለእስራኤልም ባዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁል ጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ።
41
፤ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ።
42
፤ ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች በረኞች ነበሩ።
43
፤ ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊትም ቤቱን ይባርክ ዘንድ ተመለሰ።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]