መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መጽሐፈ ዕዝራ። - Ezra
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
1
፤ የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
2
፤ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
3
፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።
4
፤ የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።
5
፤ የኤራ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት።
6
፤ ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ሁለት።
7
፤ የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
8
፤ የዛቱዕ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት።
9
፤ የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ።
10
፤ የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት።
11
፤ የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት።
12
፤ የዓዝጋድ ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት።
13
፤ የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት።
14
፤ የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት።
15
፤ የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት።
16
፤ ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።
17
፤ የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ሦስት።
18
፤ የዮራ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት።
19
፤ የሐሱም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት።
20
፤
21
፤ የጋቤር ልጆች፥ ዘጠና አምስት። የቤተ ልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት።
22
፤ የነጦፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት።
23
፤ የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
24
፤ የዓዝሞት ልጆች፥ አርባ ሁለት።
25
፤ የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።
26
፤ የራማና የጌባ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ።
27
፤ የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።
28
፤ የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት።
29
፤ የናባው ልጆች፥ አምሳ ሁለት።
30
፤ የመጌብስ ልጆች፥ መቶ አምሳ ስድስት።
31
፤ የሁለተኛውም ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
32
፤ የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።
33
፤ የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት።
34
፤ የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት።
35
፤ የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ።
36
፤ ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።
37
፤ የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት።
38
፤ የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።
39
፤ የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
40
፤ ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
41
፤ መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
42
፤ የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
43
፤ ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥
44
፤ የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፤
45
፤ የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥
46
፤ የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥
47
፤ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥
48
፤ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥
49
፤ የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥
50
፤ የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፉሰሲም ልጆች፥
51
፤ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥
52
፤ የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥
53
፤ የሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥
54
፤ የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
55
፤ የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥
56
፤ የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥
57
፤ የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።
58
፤ እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
59
፤ ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
60
፤ የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ።
61
፤ ከካህናቱም ልጆች፤ የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
62
፤ እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ።
63
፤ ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው።
64
፤
65
፤ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። ሁለት መቶም ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው።
66
፤ ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥
67
፤ ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
68
፤ በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠራ ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ።
69
፤ ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ።
70
፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹም፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]