መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መጽሐፈ ነህምያ። - Nehemiah
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
1
፤ እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥
2
፤ ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
3
፤ እኔም። ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው።
4
፤ ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር።
5
፤ አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
6
፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
7
፤ ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
8
፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።
9
፤ የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።
10
፤ የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት።
11
፤ ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት።
12
፤ የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
13
፤ የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት።
14
፤ የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ።
15
፤ የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት።
16
፤ የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት።
17
፤ የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት።
18
፤ የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት።
19
፤ የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት።
20
፤ የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት።
21
፤ የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።
22
፤ የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት።
23
፤ የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት።
24
፤ የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት።
25
፤ የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት።
26
፤ የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት።
27
፤ የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
28
፤ የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት።
29
፤ የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።
30
፤ የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ።
31
፤ የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።
32
፤ የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሦስት።
33
፤ የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት።
34
፤ የሁለተኛው ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
35
፤ የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።
36
፤ የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት
37
፤ የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ።
38
፤ የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
39
፤ ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።
40
፤ የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት።
41
፤ የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።
42
፤ የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
43
፤ ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
44
፤ መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት።
45
፤ በረኞቹ፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት።
46
፤ ናታኒም፥ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥
47
፤ የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥
48
፤ የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥
49
፤ የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥
50
፤ የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥
51
፤ የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥
52
፤ የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥
53
፤ የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥
54
፤ የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥
55
፤ የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥
56
፤ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
57
፤ የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥
58
፤ የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥
59
፤ የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች።
60
፤ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
61
፤ ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
62
፤ የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት።
63
፤ ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
64
፤ እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ።
65
፤ ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው።
66
፤
67
፤ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ሁለቱ መቶም አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው።
68
፤ ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥
69
፤ ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
70
፤ ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ።
71
፤ ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።
72
፤ የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ።
73
፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።
የገጽ ጫፍ
|
የሚቀጥለው ምዕራፍ
|
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]