መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መጽሐፈ ኢዮብ። - Job
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
1
፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2
፤ ዛሬም ደግሞ የኅዘን እንጕርጕሮዬ ገና መራራ ነው፤ እጁ በልቅሶ ጩኸቴ ላይ ከብዳለች።
3
፤ እርሱን ወዴት እንዳገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!
4
፤ በፊቱ ሙግቴን አዘጋጅ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር።
5
፤ የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደ ሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር።
6
፤ በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር።
7
፤ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር በዚያ ይከራከር ነበር፤ እኔም ከፈራጄ ለዘላለም እድን ነበር።
8
፤ እነሆ፥ ወደ ፊት እሄዳለሁ፥ እርሱም የለም፤ ወደ ኋላም እሄዳለሁ፥ እኔም አላስተውለውም፤
9
፤ ወደሚሠራበት ወደ ግራ ብሄድ አልመለከተውም፤ በቀኜም ይሰወራል፥ አላየውምም፤
10
፤ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
11
፤ እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፤ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም።
12
፤ ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።
13
፤ እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው? ነፍሱም የወደደችውን ያደርጋል።
14
፤ በእኔ ላይ የተወሰነውን ይፈጽማል፤ እንደዚህም ያለ ብዙ ነገር በእርሱ ዘንድ አለ።
15
፤ ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፤ ባሰብሁም ጊዜ ከእርሱ ፈራሁ።
16
፤ እግዚአብሔር ልቤን አባብቶታልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።
17
፤ ከጨለማው የተነሣ፥ ድቅድቁም ጨለማ ፊቴን ከመክደኑ የተነሣ አልደነገጥሁም።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]