መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መጽሐፈ ኢዮብ። - Job
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
1
፤ ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።
2
፤ የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጡ።
3
፤ እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል።
4
፤ በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።
5
፤ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፤ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6
፤ በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ። በምድር ላይ ውደቁ ይላል።
7
፤ ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
8
፤ አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
9
፤ ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።
10
፤ ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ውርጭ ተሰጥቶአል፤ የውኆችም ስፋት ይጠብባል።
11
፤ የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፤ የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፤
12
፤
13
፤ ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራችው ይዞራል።
14
፤ ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።
15
፤ በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥ የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
16
፤ ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?
17
፤ በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
18
፤ እንደ ቀለጠ መስተዋት ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
19
፤ እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና የምንለውን አስታውቀን።
20
፤ ማንም በእርሱ ላይ ቢናገር ፈጽሞ ይዋጣልና እኔ እናገር ዘንድ ብወድድ ሰው ይነግረዋልን?
21
፤ አሁንም ነፋስ አልፎ ካጠራቸው በኋላ፥ ሰው በሰማያት የሚበራውን ብርሃን ሊመለከት አይችልም።
22
፤ ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
23
፤ ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፤ በኃይል ታላቅ ነው፤ በፍርድና በጽድቅም አያስጨንቅም።
24
፤ ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፤ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]