መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መዝሙረ ዳዊት - Psalms
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150
1
በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
2
ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤
3
ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።
4
ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
5
ሥርዓትህን ለመጠበቅ፤ መንገዶቼ ይቀኑ ዘንድ እወድድ ነበር።
6
ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።
7
አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
8
ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፤ በፍጹም አትጣለኝ። ቤት
9
ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
10
በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
11
አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
12
አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።
13
የአፍህን ፍርድ ሁሉ በከንፈሬ ነገርሁ።
14
እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።
15
ትእዛዝህን አሰላስላለሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
16
በትእዛዝህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልረሳም። ጋሜል
17
ለባሪያህ መልካም አድርግ ሕያው እንድሆን፥ ቃልህንም እንድጠብቅ።
18
ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።
19
እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
20
ነፍሴ ሁልጊዜ ፍርድህን እጅግ ናፈቀች።
21
ከትእዛዛትህ የሳቱትን ትዕቢተኞችንና ርጉማንን ዘለፍህ።
22
ምስክርህን ፈልጌአለሁና። ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።
23
አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።
24
ምስክርህም ተድላዬ ነው፥ ሥርዓትህም መካሪዬ ነው። ዳሌጥ
25
ነፍሴ ወደ ምድር ተጠጋች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
26
መንገድህን ነገርሁ ሰማኸኝም፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።
27
የሥርዓትህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ተኣምራትህንም አሰላስላለሁ።
28
ከኀዘን የተነሣ ነፍሴ አንቀላፋች፤ በቃልህ አጠንክረኝ።
29
የዓመፅን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ማረኝ፤
30
የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።
31
አቤቱ፥ ምስክርህን ተጠጋሁ፤ አታሳፍረኝ።
32
ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ። ሄ
33
አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።
34
እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35
እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
36
ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን።
37
ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።
38
እንዲፈራህ ባሪያህን በቃልህ አጽና።
39
ፍርድህ መልካም ናትና የተጠራጠርሁትን ስድብ ከእኔ አርቅ።
40
እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ ዋው
41
አቤቱ፥ እንደ ቃልህ፥ ምሕረትህና መድኃኒትህ ይምጡልኝ።
42
በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ።
43
በፍርድህም ታምኛለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
44
ለዘላለም ዓለም ሁልጊዜ ሕግህን እጠብቃለሁ።
45
ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ።
46
በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤
47
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
48
እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዓትህንም አሰላስላሁ። ዛይ
49
ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ።
50
ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
51
ትዕቢተኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕግህ አልራቅሁም።
52
ከጥንት የነበረውን ፍርድህን አሰብሁ፥ አቤቱ፥ ተጽናናሁም።
53
ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኅዘን ያዘኝ።
54
በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።
55
አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን አሰብሁ፥ ሕግህንም ጠበቅሁ።
56
ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና፤ ይህች ሆነችልኝ። ሔት
57
እግዚአብሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግህን እጠብቃለሁ አልሁ።
58
በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፤ እንደ ቃልህ ማረኝ።
59
ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።
60
ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።
61
የኃጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
62
ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ።
63
እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።
64
አቤቱ፥ ምሕረትህ በምድር ሁሉ ሞላች፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። ጤት
65
አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ።
66
በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ።
67
እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።
68
አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
69
የትዕቢተኞች ዓመፅ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
70
ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።
71
ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
72
ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ
73
እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።
74
በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።
75
አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።
76
ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው።
77
ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
78
ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን በትእዛዝህ እጫወታለሁ።
79
የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።
80
እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን። ካፍ
81
ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ።
82
መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዓይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።
83
በጢስ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፤ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።
84
የባሪያህ ዘመኖች ስንት ናቸው? በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?
85
ኃጢአተኞች ጨዋታን ነገሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።
86
ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፤ በዓመፅ አሳድደውኛል፤ እርዳኝ።
87
ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።
88
እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ። ላሜድ
89
አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።
90
እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድርን መሠረትሃት እርስዋም ትኖራለች።
91
ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል።
92
ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥ ቀድሞ በጐስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር።
93
በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም።
94
እኔ የአንተ ነኝ፤ ፍርድህን ፈልጌአልሁና አድነኝ።
95
ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፤ ምስክርህን ግን መረመርሁ።
96
የሥራህን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው። ሜም
97
አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
98
ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
99
ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።
100
ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።
101
ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።
102
አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።
103
ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።
104
ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ። ኖን
105
ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
106
የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
107
እጅግ ተቸገርሁ፤ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
108
አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
109
ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
110
ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
111
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።
112
ለዘላለም ለፍጻሜውም ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን አዘነበልሁ። ሳምኬት
113
ዓመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግህን ግን ወደድሁ።
114
አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥ በቃልህም ተማመንሁ።
115
እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።
116
እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ። ከተስፋዬም አልፈር።
117
እርዳኝ እድናለሁም፥ ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ።
118
ምኞታቸው ዓመፃ ነውና ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ አጐሳቈልሃቸው።
119
የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኵሰት አጠፋሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
120
ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደንገጠ፤ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ። ዔ
121
ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።
122
ባሪያህን በመልካም ጠብቀው፤ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።
123
ዓይኖቼ ለማዳንህ፥ ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።
124
ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
125
እኔ ባሪያህ ነኝ፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።
126
ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት።
127
ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
128
ስለዚህ ወደ ትእዛዝህ ሁሉ አቀናሁ፥ የዓመፅንም መንገድ ሁሉ ጠላሁ። ፌ
129
ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው።
130
የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።
131
አፌን ከፈትሁ፥ አለከለክሁም፤ ወደ ትእዛዝህ ናፍቄአለሁና።
132
ስምህን ለሚወድዱ እንድምታደርገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመልከተ ማረኝም።
133
አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።
134
ከሰው ግፍ አድነኝ፤ ትእዛዝህንም እጠብቃለሁ።
135
በባሪያህ ላይ ፊትህን አብራ፥ ሥርዓትህንም አሰተምረኝ።
136
ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዓይኖቼ ፈሰሰ። ጻዴ
137
አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍርድህም ቅን ነው።
138
ምስክርህን በጽድቅ አዘዝህ፥ እጅግም ቅን ነው።
139
ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።
140
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባሪያህም ወደደው።
141
እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም።
142
ጽድቅህ የዘላለም ጽድቅ ነው፥ ቃልህም እውነት ነው።
143
መከራና ችግር አገኙኝ፤ ትእዛዛትህ ግን ተድላዬ ናቸው።
144
ምስክርህ ለዘላለም ጽድቅ ነው፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ። ቆፍ
145
በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ፥ ስማኝ፤ ሥርዓትህን እፈልጋለሁ።
146
ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አድነኝ፥ ምስክርህንም እጠብቃለሁ።
147
ማለዳ ጮኽሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
148
ቃልህን አስብ ዘንድ ዓይኖቼ ለመማለድ ቀደሙ።
149
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ ድምፄን ስማ፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።
150
በዓመፃ የሚያሳድዱኝ ቀረቡ፥ ከሕግህም ራቁ።
151
አቤቱ፥ አንተ ቅርብ ነህ፥ መንገዶችህም ሁሉ ቅኖች ናቸው።
152
ከዘላለም እንደ መሠረትኸው ከቀድሞ ጀምሮ ከምስክርህ የተነሣ አወቅሁ። ሬስ
153
ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም።
154
ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፤ ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
155
መድኃኒት ከኅጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።
156
አቤቱ፥ ቸርነትህ እጅግ ብዙ ነው፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።
157
ያሳደዱኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፤ ከምስክር ግን ፈቀቅ አላልሁም።
158
ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።
159
ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፤ አቤቱ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።
160
የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። ሳን
161
ገዢዎች በከንቱ አሳደዱኝ፤ ከቃልህ የተነሣ ግን ልቤ ደነገጠብኝ።
162
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
163
ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፤ ሕግን ግን ወደድሁ።
164
ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።
165
ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም።
166
አቤቱ፥ ማዳንህን ተስፋ አደርግሁ፥ ትእዛዛትህንም ጠበቅሁ።
167
ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች እጅግም ወደደችው።
168
መንገዶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸውና ትእዛዝህንና ምስክርህን ጠበቅሁ። ታው
169
አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።
170
ልመናዬ ወደ ፊትህ ትድረስ፤ እንደ ቃልህ አድነኝ።
171
ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ።
172
ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና አንደበቴ ቃልህን ተናገረ።
173
ትእዛዛትህን መርጫለሁና እጅህ የሚያድነኝ ይሁን።
174
አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ተድላዬ ነው።
175
ነፍሴ ትኑርልኝ ታመሰግንህማለች፥ ፍርድህም ይርዳኝ።
176
እንደ ጠፉ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባሪያህን ፈልገው።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]