መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መዝሙረ ዳዊት - Psalms
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150
1
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር። 1 ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።
2
ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
3
አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፤ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።
4
እግዚአብሔርን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው።
5
አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።
6
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም፤ ሥጋን አዘጋጀህልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻህም።
7
በዚያን ጊዜ አልሁ። እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤
8
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
9
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ፤ እነሆ፥ ከንፈሮቼን አልከለክልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ።
10
እውነትህንም በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥ ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም።
11
አቤቱ፥ አንተ ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።
12
ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና፤ ኃጢአቶቼ ያዙኝ፥ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።
13
አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
14
ነፍሴን ለማጥፋት የሚወድዱ ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወድዱ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይጐስቍሉም።
15
እሰይ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።
16
አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር። እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን ይበሉ።
17
እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፥ ጌታ ግን ያስብልኛል፤ አንተ ረዳቴና መድኃኒቴ ነህ፤ አምላኬ ሆይ፥ አትዘግይ።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]