መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
ትንቢተ ኤርምያስ - Jeremiah
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
1
ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፤
2
በሴዴቅያስም በአሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች።
3
የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
4
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰልፈኞቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ፤ በዓረባም መንገድ ወጡ።
5
የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፥ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፤ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
6
የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዓይኑ ፊት በሪብላ ገደላቸው፤ የባቢሎንም ንጉሥ የይሁዳን ከበርቴዎች ሁሉ ገደለ።
7
የሴዴቅያስንም ዓይን አወጣ፥ ወደ ባቢሎንም ይወስደው ዘንድ በሰንሰለት አሰረው።
8
ከለዳውያንም የንጉሡንና የሕዝቡን ቤቶች በእሳት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።
9
የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
10
አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያን ጊዜ ሰጣቸው።
11
-
12
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ። ውሰደውና በመልካም ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ክፉን ነገር አታድርግበት ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ።
13
የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፥ ናቡሽዝባንም ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ላኩ፤
14
ኤርምያስንም ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፥ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
15
በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ።
16
ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።
17
በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም።
18
ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፥ በእኔ ታምነሃልና፥ ይላል እግዚአብሔር።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]