መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን - Songs of Solomon
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
1
፤ ሌሊት በምንጣፌ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፤ ፈለግሁት አላገኘሁትም።
2
፤ እነሣለሁ በከተማይቱም እዞራለሁ፥ ነፍሴ የወደደችውን በጎዳናና በአደባባይ እፈልጋለሁ፤ ፈለግሁት አላገኘሁትም።
3
፤ ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።
4
፤ ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት፥ ያዝሁትም ወደ እናቴም ቤት ወደ ወላጅ እናቴም እልፍኝ እስካገባው ድረስ አልተውሁትም።
5
፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሡትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አምላችኋለሁ።
6
፤ መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?
7
፤ እነሆ፥ የሰሎሞን አልጋ ናት፤ ከእስራኤል ኃያላን ስድሳ ኃያላን በዙሪያው ናቸው።
8
፤ ሁሉም ሰይፍ የያዙ ሰልፈኞች ናቸው፤ በሌሊት ከሚወድቀው ፍርሃት የተነሣ ሰው ሁሉ ሰይፉ በወገቡ አለ።
9
፤ ንጉሡ ሰሎሞን መሸከሚያን ከሊባኖስ እንጨት ለራሱ አሠራ።
10
፤ ምሰሶቹን የብር፥ መደገፊያውንም የወርቅ፥ መቀመጫውንም ሐምራዊ ግምጃ አደረገ፤ ውስጡ በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ፍቅር የተለበጠ ነው።
11
፤ እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት፥ ውጡ፤ እናቱ በሠርጉ ቀንና በልቡ ደስታ ቀን ያደረገችለትን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን እዩ።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]