መነሻ
| |
ድምጽ
| |
ማውጫ
| |
ምዕራፎች
ኦሪት ዘጸአት - Exodus
ምዕራፍ:
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
1
፤ ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።
2
፤ ሌባው ቤት ሲምስ ቢገኝ፥ እርሱም እስኪሞት ቢመታ፥ በመታው ሰው ላይ የደም ዕዳ አይሆንበትም።
3
፤ ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት፤ ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ።
4
፤ የሰረቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬም ወይም አህያ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል።
5
፤ ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥ የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም ወይኑ ይካስ።
6
፤ እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ።
7
፤ ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ ስለ አንድ ሁለት ይክፈል።
8
፤ ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈራጆች ይቅረብ፥ እጁንም በባልንጀራው ከብት ላይ እንዳልዘረጋ ይማል።
9
፤ ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም። ይህ የእኔ ነው ቢል፥ ክርክራቸው ወደ ፈራጆች ይድረስ፤ ፈራጆቹም የፈረዱበት እርሱ ለባልንጀራው በአንድ ሁለት ይክፈል።
10
፤ ሰው በባልንጀራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥
11
፤ በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት መሐላውን ይቀበል፥ እርሱም ምንም አይክፈል።
12
፤ ከእርሱም ዘንድ ቢሰረቅ የጠፋውን ያህል ለባለቤቱ ይመልስ።
13
፤ ተቧጭሮም ቢገኝ ለምስክር ያምጣው፤ በመቧጨሩም ምክንያት አይክፈል።
14
፤ ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ፈጽሞ ይክፈለው።
15
፤ ባለቤቱ ግን ከእርሱ ጋር ቢኖር አይክፈል፤ ቢከራየው በክራዩ ይግባ።
16
፤ ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያስታት፥ ከእርስዋም ጋር ቢተኛ፥ ማጫዋን ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት።
17
፤ አባትዋም እርስዋን እንዳይሰጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደናግል ማጫ ያህል ብር ይክፈላት።
18
፤ መተተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድላት።
19
፤ ከእንስሳ ጋር የሚረክስ ፈጽሞ ይገደል።
20
፤ ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።
21
፤ እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና ስደተኛውን አትበድለው፥ ግፍም አታድርግበት።
22
፤ መበለቲቱንና ድሀ አደጎቹን አታስጨንቁአቸው።
23
፤ ብታስጨንቁአቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ እኔ ጩኸታቸውን ፈጽሞ እሰማለሁ፤
24
፤ ቍጣዬም ይጸናባችኋል፥ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለት፥ ልጆቻችሁም ድሀ አደጎች ይሆናሉ።
25
፤ ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለወገኔ ለድሀው ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁን፥ አራጣም አትጫንበት።
26
፤ የባልንጀራህን ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤
27
፤ ሥጋውን የሚከድንበት እርሱ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ።
28
፤ ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብህንም አለቃ አትርገመው።
29
፤ ነዶህንም የወይንህንም ጭማቂ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኵር ትሰጠኛለህ።
30
፤ እንዲህም በበሬዎችህና በበጎችህ ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፥ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
31
፤ ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በምድረ በዳ አውሬ የቧጨረውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት።
የገጽ ጫፍ
| |
የሚቀጥለው ምዕራፍ
| |
ማውጫ
|
መነሻ
Full online version
here
[with search engine, multilingual display and audio Bible]